ከሳምንት በፊት በተለይም የጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ት ቤት "የጸጥታ ኃይሎች በህወሓት ላይ ርምጃ እንዲወስዱ አቅጣጫ ተቀምጧል" የሚል መግለጫ ከመስጠቱ በፊት የተደረገ ቃለ መጠይቅ ነው። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች መኖራቸውን የተናገሩ ሲሆን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና መገናና ብዙኃንን በወገንተኝነት ከሰዋል። ሙሉ ቃለ መጠይቁ በዚህ መልኩ ቀርቧል። ቢቢሲ፡ ጦርነቱ በስንት ግንባር ነው እየተካሄደ ያለው? ዶ/ር ፋንታ፡ ጦርነቱ በሁሉም አማራ ክልል ከትግራይ ክልል ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች የሚደረግ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ አማራ ክልል ውስጥ ዘልቆ በመግባት ነው እየተካሄደ ያለው። በሰሜን በኩል ከጠለምት ጀምሮ እስከ አፋር ድንበር ድረስ ይዘልቃል።በብዙ መቶ ኪሎ ሜትሮች የሚሸፍን ውጊያ ነው እየተደረገ ያለው። ቢቢሲ፡ የጦርነቱን ሁኔታ እንዴት ይገልጹታል? ዶ/ር ፋንታ፡ ህወሓት ሙሉ ወረራ ነው እያደረገብን ያለው። በሁሉም ግንባሮች ያልተገደበ ጥቃት ነው እየፈጸመ ያለው። የተናጠል ተኩስ አቁሙን በሚጻረር መልኩ ነው ጥቃቱን እየፈጸመ ያለው። ዜጎች በየቀኑ ከግጭቱና ከግድያው ለማምለጥ በገፍ እየተሰደዱ ነው። ቢቢሲ፡ አሁን ውጊያ እንዳለ ነግረውናል እና ተኩስ አቁሙ አለ ማለት እንችላለን? ዶ/ር ፋንታ፡ መጀመሪያ መንግሥት የተኩስ አቁሙን ያደረገው በተናጠል ነበር። ነገር ግን ህወሓት ያለማቋረጥ ጥቃት ሲፈጽም እና ጭፍጨፋ ሲፈጽም ማቆሚያው የት ነው? ዜጎች በጠራራ ፀሐይ እየተጨፈጨፉ ነው። ተኩስ አቁሙ መከበር ነበረበት። እናም መንግሥት የመከላከል ሥራ ነው እየሰራ ያለው። ዜጎቻችንን እየተከላከልን ነው ያለነው። ከዚያ ያነሰም ሆነ የገፋ ነገር እያደረግን አይደለም። አሁን እያወራን ባለበት ወቅት ዜጎች ያለማቋረጥ ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው። ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮችን እያስተናገድን ነው። አዲስ ባገረሸው ጦርነት ከ2 መቶ ሺህ በላይ ዜጎች ከራሳቸው የትውልድ አካባቢ ተፈናቅለዋል። ስለዚህ ውይይቱንም ቢሆን ለማድረግ የመጀመሪያውና ብቸኛው መንገድ የተጣለውን ተኩስ አቁም ማክበር ነው። ቢቢሲ፡ ህወሓት ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ የተኩስ አቁም እንደማያደርግ ተናግሯል። እናንተ ለዚህ ምላሻችሁ ምንድን ነው? ዶ/ር ፋንታ፡ የጠየቅከኝን ጥያቄ ራስህ መልሰኸዋል። ዜጎች እየተጨፈጨፉ እና እየተፈናቀሉ ዝም ብለን ተኩስ ማቆም እንዳለብን የምታስብ አይመስለኝም። ብቸኛው መንገድ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መጀመሪያ ተኩስ አቁሙን መቀበል አለባቸው። ቢቢሲ፡ ከ200 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንዳሏችሁ ነግረውናል። ምን አይነት ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው አሁን? ዶ/ር ፋንታ፡ ከሰብአዊ ኤጀንሲዎች ጋር እየተወያየን ነው። ለተፈናቃዮች የእርዳታ ድርጅቶች እኩል ትኩረት እየሰጡ አይደለም። ሳስተምረው ከነበረው እና ካለኝ እውቀት ጋር የሚጻረር በሰብአዊነት ላይ አድሏዊነት እያየሁ ነው። የአማራ ክልል ተፈናቃዮች ተገቢው ሰብዓዊ እርዳታ እየደረሰላቸው አይደለም። እየቀረበ ያለው እርዳታ በቂ አይደለም። እርዳታ ከሚያቀርቡ ድርጅቶች ጋር ተነጋግረናል። ፍትሃዊ አቅርቦት አለመኖሩን አስረድተናል። ነገር ግን እስካሁን ምንም የተቀየረ ነገር የለም። ይህ እስከሚስተካከል እየጠበቅን ነው። ቢቢሲ፡በርካታ ወጣቶች የአማራ ልዩ ኃይልን ወይም መከላከያን እየተቀላቀሉ እንደሆነ እያየን ነው። በቁጥር ምን ያህል ወጣት ሊቀላቀል ይችላል? ይህ ሁኔታስ በጦርነቱ ቅርጽ ላይ ምን አይነት ለውጥ ያመጣል? ዶ/ር ፋንታ፡ የጠራነው ራሱን/ራሷን እንዲከላከል/እንድትከላከል ሁሉንም ሕዝባችንን ነው። ይህ ጥሪ ለእያንዳንዱ ዜጋችን ራሱን እንዲከላከል የተደረገ ጥሪ ነው። ይህ በሌሎች ላይ የታወጀ ጦርነት አይደለም። ራስን የመከላከል ጥሪ ነው። ስለዚህ ጥሪውን ለእያንዳንዱ ዜጋ ስላደረግን ይህንን ያክል ብዬ በቁጥር ልገልጽልህ አልችልም። ምናልባትም በሚሊዮኖች ሊሆን ይችላል። ቢቢሲ፡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተለይም ደግሞ የአሜሪካ መንግሥት የአማራ ልዩ ኃይል አማራና ትግራይ በይገባኛል በሚወዛገቡበት አካካቢ [ወልቃይትና አካባቢዎቹ] ይውጡ ብለዋል። የእናንተ ምላሽ ምንድን ነው? ዶ/ር ፋንታ፡ በዚያ ቦታ የአማራ ኃይል የሚባል የለም። ያሉት የፌደራል መንግሥት መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ክልልን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች ልዩ ኃይሎች ናቸው። በሁሉም አካባቢዎች የተሰማራው ኃይል የሚመራው በፌደራል መንግሥት ዕዝ ስር ነው። ቢቢሲ፡ ይህ ጦርነት መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። በተለይም የተለያዩ ክሶች ይቀርባሉና በዚህ ጉዳይ ላይ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚሉት ነገር አለ? የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስለማይካድራው ጭፍጨፋ ትንፍሽ አላለም። ይህ እንደ ሰው በጣም አሳዛኝ ነው። በህወሓት ጭፍጨፋ ሰለባ ሆነው ሳለ ዝም መባላቸው በጣም ያስከፋል። በሰሜን ወሎ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ዋግኽምራ እና አፋር ክልል ስለሚፈናቀሉት ዜጎች የሚሉት ነገር የለም። ይህ ምን ማለት ነው? በእውነት ለኢትዮጵያ የሚጨነቁ ከሆነ በሚሰጧቸው መግለጫዎች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። አንዳንድ ጊዜ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የሚሰጡ መደማደሚያዎች እጅግ አሳዛኝ ናቸው። ምክንያቱም ምንም አይነት ማጣሪያ ሳያደርጉ የራሳቸውን ድምዳሜ ይሰጣሉ። ይህ ለተጎጅዎች ሌላ ጉዳት ነው። ዶ/ር ፋንታ፡ በዘገባችሁ አካታችሁት እንደሆነ ባላውቅም ባለፈው መጋቢት እና ሚያዚያ በሰሜን ሸዋ ዞን እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በርካታ ሰዎች ተፈናቅለዋል፣ በምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም፣ በደቡብ ጎንደር፣ በሰሜን እና ደቡብ ወሎ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በሚነሱ ግጭቶች ምክንያት ተፈናቅለው ይገኛሉ። ቢቢሲ፡ በወልቃይት አካባቢ የትግራይ ተወላጆች ተፈናቅለዋል፣ ጥቃትም ደርሶባቸዋል በተለይ ግድያ ተፈጽሞ አስከሬናቸው ተከዜ ወንዝ ላይ ተጥሏል በሚል ለሚቀርብው ክስ ምላሻችሁ ምንድን ነው? ዶ/ር ፋንታ፡ በእንደዚህ አይነት ድራማ እና ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል የራሱን ዜጎች በመግደል ትህነግ በሚገባ የሚታወቅና የሰለጠነ ነው። እናም ይህ የድራማው እንድ አካል እንደሆነ እጠረጥራለሁ። በትግራይ ያለው የእርዳታ አቅርቦትና ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮች ከሰሜን ወሎ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደሴ የገቡ ተፈናቃዮች ሁኔታ ቢቢሲ፡ ይህ ግጭት ከተጀመረ ዘጠኝ ወር እየሆነው ነው። እና በብዙ ዘርፎች ላይ ተጽዕኖ ነበረው። ግጭቱ በአጭር ጊዜ ሊቋጭ የሚችልበት መንገድ አለ ብለው ያምናሉ? ዶ/ር ፋንታ፡ ለምን መፍትሔ አይኖርም? በዓለም ላይ የማይቻል ነገር የለም። የማይቻል የምናደርገው የግጭቱ ተዋንያን ነን። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በቅርበት ከሰራ እና ህወሓትን የሰላም አማራጮችን እንዲያማትር ከጠየቀ ችግሩን የማንፈታበት መንገድ ላይኖር አይችልም። የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግን ይህንን እየሰማ ዝምታን መርጧል። አሁን ለጊዜው የማላስታውሰው አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም እውነታውን ሰሞኑን ተናግሯል። ይህ ጥሩ ጅምር ነው። ከችግሩ የመውጫ ትክክለኛ መንገዳችን እውነት ብቻ ነው። ቢቢሲ፡ ህወሓት በቅርቡ የተኩስ አቁሙን ተቀብሎ ወደ ድርድር ይመጣል ያምናሉ? ዶ/ር ፋንታ፡ በህወሓት ቦታ ሆኜ መናገር አልችልም። ህወሓት በየጊዜው ሃሳቡን ይቀያይራል። ይህ የራሳቸው ጉዳይ ነው። ቢቢሲ፡ ህወሓት ጦርነቱን ቢቀጥል ምን ታደርጋላችሁ? ዶ/ር ፋንታ፡ ሕዝባችንን ከታወጀበት ጦርነት መከላከላችንን እንቀጥላለን። ያለን ብቸኛው አማራጭ እሱ ነው። በእኛ ላይ ጦርነት ማወጁን ህወሓት በይፋ ግልጽ አድርጓል ምንም እንኳ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ምንም ነገር ማለት ባይችልም። ህወሓት ግን ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ ሲዖል እንደሚሄድ ነግሮናል።ይህንን ዝም ብለን አንመለከትም። አንተስ እንደ ጋዜጠኛ በዚህ ደረጃ ሕዝባችን ላይ ጥቃት የሚፈጽምን፣ የሚያፈናቅልን እና ያልተገደበ የበቀል ፍላጎቱን ለማሟላት በደል የሚፈጽምን አካል ምን ልንለው እንድንችል ትጠይቀኛለህ? ይህንን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይገነዘባል ግን ምንም አይልም።
በአማራ ብሔራዊ ክልል ከስደት ተመላሾችን በILO ፕሮጀክት ለማቋቋም የተከናወኑ ተግባራትና ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ፡፡ ከስደት ተመላሾች በክልላቸው ሰርተው መኖር የሚያስችላቸውን አቅም ለመፍጠር፣ የስልጠናና ሌሎች ድጋፎችን ለማድረግ በተዘጋጀው ፕሮጀክት አፈጻጸም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተደረገውን ውይይት የመሩት የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ያየህ አዲስ ሲሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያከናወኑትን ተግባራትና ያጋጠሙትን ችግሮች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ እስካሁን ድረስ 3,397 ለሚሆኑ ተመላሾች የኢንተርፕሪነር ስልጠና መውሰዳቸውንና 1582 ለሚሆኑ ተመላሾችም የሙያ ስልጠና መሰጠቱን የአብክመ ሙያ፣ ቴክኒክና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አሳውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለ796 ተመላሾች 19,779,260 ብር ከአብቁተ ብድር መውሰዳቸውን በውይይቱ ተገልጿል፡፡ የባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ አለመስራትና የተለያዩ ስልጠናዎችን ከወሰዱት ተመላሾች ውስጥ የደረሱበትን ደረጃ በመከታተል ውስንነት መኖሩንም ተገምግሟል፡፡ በቀጣይም ፕሮጀክቱ ተግባራዊ በሚደረግባቸው ዞኖችና ወረዳዎች አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አብራርተዋል፡፡
መጋቢት 07/2010 ዓ.ም የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
|
የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና የዞን አስተዳደር ጽ/ቤቶች የ2010 በጀት አመት የመጀመሪያው የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ፡፡ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ከዞን አስተዳደርና ከንቲባ ጽ/ቤቶች ጋር በባህር ዳር ከተማ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ ውይይት የሚደረግባቸው ርዕሰ ጉዳዮች፡- - >የፕላን ኮሚሽን አደረጃጀትና የአስተዳደር ጽ/ቤቶች ቅንጅታዊ አሠራር> - >የዞንና የከንቲባ አስተዳደር ጽ/ቤቶች የሠው ኃይል አደረጃጀት ስምሪትና የጥያቄ አቀራረብ> - >የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አስፈላጊነትና ክልላዊ ሁኔታዎች> - >የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች መንስኤና ውጤት ክልላዊ ገጽታ> - >የገጠር ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ለየደረጃው አስተዳደር ጽ/ቤቶች ስራ መቃናት ያለው ፍይዳ፤ አስተዳደርና አጠቃቀም> - >የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት> - >የዞንና የከንቲባ ጽ/ቤቶች ሪፖርት> - >የቀጣይ ወራት ትኩረት አቅጣጫዎች ሲሆኑ፤> የምክክር መድረኩ ከመጋቢት 12-14/2010 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡ መጋቢት 12/2010 ዓ.ም የዳያስፖራና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
የፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል ለህዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት በሚሻሻልበት ሁኔታ መስተዳድር ም/ቤቱ ውሳኔ አስተላለፈ የአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ በሆስፒታሉ የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎት ለማሻሻልና መከናወን ስላለባቸው ተግባራትና በክልሉ ውስጥ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን የተሰሩት ስራዎች በርካታ ችግሮችን እንዲፈቱ በዝርዝር ለመስተዳድር ም/ቤቱ አቅርቧል፡፡ነገር ግን በየአመቱ ወደ ሆስፒታሎች የሚሔደው ተገልጋይ ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ብዙ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው በዝርዝር ቀርቧል፡፡ በዚህም መሰረት፡- Ø >ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የህክምና ትምህርት እየሰጡ ያሉበት ሆስፒታሎች ላይ ለአገልግሎት መስጫ የሚሆን ማስፋፊያዎችን በፕላናቸው ውስጥ አካተው እንዲሰሩ ለማድረግ ከዩኒቨርስቲዎች ፎረም ላይ መተማመን መድረስ እንደሚያስፈልግ፤> Ø >በሪፈራል ሆስፒታሎች ተጨማሪ ማስፋፊያዎች እንዲኖሩ ፤> Ø >በተለያዩ ምክንያቶች የወጡ ወጭዎች ለተቋማቱ የሚመላለሱበት ሁኔታ እንዲመቻች፤> Ø >በሪፈራል ሆስፒታሎች የመጀመሪያው የህሙማን ቅብብሎሽ አሰራር ሲጀመር የሚያጋጥመውን ግፊት ከወዲሁ በመገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፤> Ø >ለፈለገ ህይወት ጊዚያዊ የሆነ በፍጥነት የሚደርስ ግንባታ ለእናቶችና ህጻናት ድንገተኛ ክፍል እንዲገነባ ማድረግ፣> Ø >የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር ማድረግ፣> Ø >የአዲስ አለምን ሆስፒታል ወደ ጠቅላላ ሆስፒታል ማሳደግ፣> Ø >ተዘጋጅቶ በሚቀርበው የአገልግሎት መስጫ የዋጋ ተመን እንደሚያስፈልግ ቤቱ አይቶ እንዲያፀድቅ በሚሉ ጉዳዮች መስተዳድር ምክር ቤቱ ሠፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ፡- በክልሉ ውስጥ በርካታ ሆስፒታሎች ተከፍተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ቢሆኑም የተገልጋዩ ፍሰት ማስተናገድ ከማይቻልበት ሁኔታ ላይ የመድረስ /የመጨናነቅ/ መድረስና በአገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ አየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን በመረዳት ለችግሩ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የክልሉ መንግስት የሚቻለውን ሁሉ እንደሚደረግ መስተዳድር ም/ቤቱ ወስኗል፡፡>
|