የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

በኮምቦልቻ ለዘመናዊ አገልገሎት እና ለሰው ተኮር ተግባራት የተሰጠው ትኩረት የሚደነቅ ነው።

ዛሬ የኮምቦልቻ ሪጆፖሊታን ከተማ አስተዳደር የዲጂታል አገልግሎትና የዘመናዊ የሥራ ቦታ እድሳትና ሰው ተኮር ተግባራትን ተመልክተናል።

የከተማ አስተዳደሩ ህንጻ የስማርት ሲቲ እሴቶችን ባሟላ መልኩ ታድሷል። ህንጻው ዲጅታል አሰራርን ለመተግበር በሚያስችል መልኩ መደራጀቱ አገልግሎትን ለማዘመን አጋዥ አቅም ይፈጥራል።

ሌላው በከተማዋ የተመለከትነው በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች ተገንብተው ለነዋሪዎች የተላለፉ መኖሪያ ቤቶችን ነው፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ባለሀብቶችንና ህብረተሰቡን በማስተባበር ባስገነባቸው ሁለት የመኖሪያ ብሎኮች ለአቅመ ደካሞችና አረጋውያን ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን አስረክቧል።

በኮምቦልቻ የጎበኘናቸው የዲጂታል የከተማ አገልግሎት ፕሮጀክትና ሰው ተኮር ተግባራት በከተሞቻችን እየተገበርናቸው ያሉ የአካታች ልማት ማሳያዎች ናቸው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top