The Building Management Office
Building Management
VISION /ራዕይ/
“በ2025 ዓ.ም ደ/ታቦር ከተማን የብልፅግና ማዕከላት በማድረግ እና ተወዳዳሪ እና ምርታማ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በመገንባት፣ በደ/ታቦር ከተማ የሚገነቡ ህንፃዎች የህንፃ ህጉን የጠበቁ፤ የህዝቡን ደህንነትና ጤንነት ያረጋገጡ እና የከተማውን ደረጃ የጠበቁ ሆነው ማየት”
MISSION /ተልዕኮ/
- በከተማው የሚገነቡ ህንፃዎች የከተማዋን ደረጃ ጠብቀው የህብረተሰቡን ፍላጎት ያሟሉ የህዝብን ደህንነት እና ጤንነት ያረጋገጡ እንዲሆኑ መከታተል፣
- በግልና በመንግሥት የሚገነቡ የህንፃ ግንባታዎች በተያዘላቸው ወጪ፣ ጊዜና ጥራት መሠረት ተጠናቀውና የመጠቀሚያ ፈቃድ አግኝተው ለህዝቡ ጥቅም እንዲውሉ ማድረግ፣
- ሁሉም ፈፃሚ፣ አስፈፃሚ እና ማህበረሰቡ የህንፃ አዋጁን፣ ደንቡንና መመሪያውን አውቆ እንዲፈፅም ክትትል ማድርግ፣
- የዘርፉን ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበርና በማቀናጀት ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት፣
በህንፃ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው ሥርዓት በመፍጠር እና የኮንስትራክሽን ተዋናዮችን አቅም በመገንባት ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መገንባት፣
CORE VALUES / እሴቶች/
- ሀቀኝነት፣ ግልጸኝነት፣ ተጠያቂነት፤
- የአሠራር መርህን ተከትሎ መስራት፣
- ለውጤታማነትና ለሥራቅልጥፍና ዘወትር መትጋት፣
- ሁሌም በማያቋርጥ የመማርና የመማማር ሂደት ላይ መሆን፣
- ለህዝብ ጥቅም ቅድሚያ መስጠት እና ሁሉንም ሰው እኩል ማየትና
- የተለያዩ ሃሳቦችን በአግባቡ ማስተናገድ፤
- ወጪ ቆጣቢ አሠራርን መከተል፤
- የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባርን አጥብ ቆመታገል፤