Women and Childers Affaires Department
Women and Childers Affaires
VISION /ራዕይ/
- በ2022 የሥርዓተ ፆታ እኩልነት የተረጋገጠበት እና የማህበራዊ ጥበቃ የተስፋፋበት ከተማ ሆኖ ማየት፡፡
MISSION /ተልዕኮ/
- በሴቶች፣ ህጻናት እና አካል ጉዳተኞች ላይ ጉዳት እያደረሱ ያሉ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች፣ የተዛቡ አመለካከቶችና ለማህበራዊ ችግር ተጋላጭነትን ለማስወገድ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችና ስልጠና መስጠት፣
- ሴቶች፣ ህጻናት፣ አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች ተደራጅተው ለመብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸው እንዲታገሉ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣
- የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓትን በመዘርጋት እና የዜግነት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በማሳደግ በአስቸጋሪ ሁኔታ ለሚገኙ ህጻናት፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞች ድጋፍና እንክብካቤ ማድረግ፣ እንዲሁም በሚወጡ ፖሊሲዎች፣ ህጎች፣ ፕሮግራሞች፣ ፕሮጀክቶችና በሚዘጋጁ ዕቅዶች ሙሉ ተሳታፊና ተጠቃሚ መሆናቸውን ማረጋገጥና የፈጻሚ ተቋማትን አቅም መገንባት ነው፡፡
CORE VALUES / እሴቶች/
- ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለአረጋውያን የላቀ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንተጋለን፣
- ምቹና ሰራተኛው የሚተማመንበት ተመራጭ ተቋም እንፈጥራለን፣
- ለሴቶች፣ ለህጻናት፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለአረጋውያን አገልጋይ በመሆናችን እንኮራለን፣
- የማህበራዊ ችግሮችን ለመከላከል እንተጋለን፣
- በዕውቀትና በዕምነት መምራትና መስራትን ባህላችን እናደርጋለን፣
- ልዩ ድጋፍና ልዩ ትኩረት ለሚሹ በሚል መርህ እናምናለን፣