Special support advisor
VISION /ራዕይ/
- የዴሞክራሲ ተቋማትንና የመልካም አስተዳደር አደረጃጀትን ማጠናከር፣ የክትትልና፣ የድጋፍ ተግባራትን ማከናዎን።
- ልማትን የሚያፋጥኑ ህጎችን አፈጻጸም መከታተል
- ለመንግሰታዊ ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ዜጎችና ለከፍተኛው አመራር ሁለንተናዊ የድጋፍና የመረጃ አገልግሎት መስጠት
MISSION / ተልዕኮ/
- ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የተረጋገጡበት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነበት፣ በሁሉም የልማት መስኮች ፈጣን እድገት የተመዘገበበትና ድህንነትን ታሪክ ያደረገ ከተማ አስ/ ተፈጥሮ ማየት።
CORE VALUES / እሴቶች/
- የጽ/ቤቱ ሰራተኞች የሚከተሏቸው የሥራ መርሆዎችና እሴቶች፦
- በየደረጃው ላለው አመራር የተሟላ የድጋፍ አገልግሎት ለመስጠት ተግተን እንሰራለን፣
- ህዝባዊ ወገንተኝነታችንን በስራ እናረጋግጣለን
- የህግ የበላይነትን እናከብራለን፣
- የባለጉዳዮቻችን ጥያቄ በጥሞናና በትህትና አዳምጠን ወቅታዊና ተገቢ ምላሽ እንሰጣለን፣
- በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የሥርዓተ ጾታ መርህን እንከተላለን፣
- የሕብረተሰቡንና የመ/ቤቱን ሠራተኞች ዲሞክራሲያዊ ተሣትፎ ያረጋገጠ አሰራር እንከተላለን፣
- የግለሰቦችን ጥረትና ተነሳሽነት እንዲጎለብት እናበረታታለን፣
- ተደጋግፎ የመስራት ባህልና መተማመን በመ/ቤቱ ውስጥ እንዲሰፍን እናደርጋለን።