Geogeraphy
መልካም ምድራዊ አቀማመጥ
ከተማዋ ወደ ሪጂዮ ፖሊታን ከተማነት ለማደግ በነበራት ጥያቄ ከሰኔ 25/2014 ዓ.ም ጀምሮ ሪጅዮ ፖሊታን ከተማነትን ያገኘች ከተማ ነች ፣ከተማዋ ከአዲሰ አበባ 667 ኪ/ሜትር፣ከባህር ዳር 103 ኪ/ሜትር፣ከጎንደር 153 ኪ/ሜትር እርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ ከተማዋም በአራቱም አቅጣጫዎች የፋርጣ ወረዳ ያዋስናታል፡፡
የቆዳ ስፋቷም አሁን ባላት የወሰን ክልል 12109.38 ሄ/ር ስፋት የአላት ሲሆን ወደ ፊት በተሸሻለው የከተሞች ፈርጅ መወሰኛና ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 196/2013 ክፍል ሶስት አንቀጽ 8/1/1 መሰረት የሪጂዮ ፖሊታት ከተማ አስተዳደሮች ወሰን በዙሪያው እስከ 30 ኪ/ሜ የአየር ራዲየስ የሚገኘውን መልክዓ ምድራዊ ክልልና በውስጡ የሚገኘውን ነዋሪ ህዝብ ማጠቃለል እንደምችል ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም ይህን መሰረት በማድረግ ወደፊት የከተማው የሰው ሃይል አደረጃጀትና የበጀት አቅሙ እያደገ ሲሄድ በጥናት ላይ ተመስርቶ በእቅድ ይዞ ወሰኑን በደንቡ መሰረት የማስፋት ስራ ይሰራል፡፡
የደ/ታቦር ከተማ ከባህር ወለል በላይ በ2,200 ሜትር ከፍታ የምትገኝ ሲሆን የከተማዋ መልካም ምድር 14% ተራራማና 66% ወጣ ገባ 20% ሜዳማ ነዉ፡፡
የከተማዋ አየር ንብረት ወይና ደጋና እጅግ ለጤና ተስማሚ ስትሆን አመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን 1553.7 ሚሊ ሌትር እና አመታዊ የሙቀት መጠን 15 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነዉ፡፡