የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ በተገኙበት ለክልሉ ፖሊስ አባላትና አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በባህርዳር ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።
ስልጠናው ከጂኦ ስትራቴጂካዊ ኩስምና ወደ ታደሰ ቁመና በሚል መሪ ሃሳብ እየተሰጠ ስለመሆኑ ተገልጿል።
ስልጠናው የክልሉ ፖሊስ የመፈጸም አቅምን ለማሳደግ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ነው።
ስልጠናው የክልሉን የፖሊስ አባላትን እና አመራሮችን አቅም ከማሳደግ ባሻገር ለክልሉ ሆነ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ሰላም እና ልማት መረጋገጥ የሚያግዝ ስለመሆኑም ተጠቁሟል።
በስልጠናው የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር)፣ ምክትል ኮሚሽነሮች እንዲሁም ስትራቴጂክ እና ከፍተኛ የፖሊስ አመራሮች ጭምር እየተሳተፉ ይገኛሉ።

