አስደማሚው የፋሲል ግንብ ግቢ

ፋሲል ግንብ የተሠራው በአጼ ፋሲለደስ ዘመነ መንግስት 1632 ዓ.ም ነው። ለታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ምልክት ነው። ግቢው 70 ሺህ ስኩዌር ሜትር ስፋት አለው።

በየዓመቱ በመቶ ሺህዎች የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኝዎች ይጎበኛል። ፋሲል ግንብ አገልግሎታቸውን የሚወክል ስያሜ ያላቸው 12 በሮች አሉት።

👉12 በሮችም፦

🚪 ፊት በር ወይም ጃን ተከል በር ንጉሰ ነገስቱ የሚገቡበት በር ነው፡፡

🚪 ወንበር በር ዳኞች የሚገቡበት በር ነው፡፡

🚪 ራስ በር መሳፍንት እና መኳንንት የሚገቡበት በር ነው፡፡

🚪 አዛዥ ጠቋሬ በር የግቢው አዛዦች የሚገቡበት በር ነው፡።

🚪 አደናግር በር ጥጥ ፈታዮች የሚገቡበት በር ነው፡፡

🚪 ኳሊ በር የነገሥታት አጃቢዎች የሚገቡበት በር ነው፡፡

🚪 እምቢልታ በር የሙዚቃ መሳሪያ የሚጫወቱ ሰዎች የሚገቡበት በር ነው፡፡

🚪 ባልደራስ በር የቤተመንግሥት ፈረሶች አለቃ የሚገቡበት በር ነው፡፡

🚪 እርግብ በር ስጦታዎች የሚገቡበት በር ነው፡፡

🚪 ተስካር በር ለሙታን መታሰቢያ የሚመጡ ሰዎች የሚገቡበት በር ነው፡፡

🚪 እንኮይ በር እትጌ ምንትዋብ እና ልዕልት እንኮየ የሚገቡበት በር ነው፡፡

🚪 እቃ ግምጃ ቤት በር ወደ ግምጃ ቤት ማርያም የሚያስኬድ በር ነው፡፡

👉አስደማሚው የፋሲል ግንብ ግቢና ኪነህንጻ ነባር ይዘቱን በጠበቀ መንገድ እድሳት ተደርጎለት ለጎብኝዎች ክፍት ሆኗል። የፋሲል ግንብን ይጎብኙ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top