ኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) መልዕክት

ዛሬ ጠዋት በአማራ ክልላዊ መንግሥት ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር መቀመጫ በሆነችው ከሚሴ ተገኝቼ ለሕዝቡ መልዕክት አስተላልፌያለሁ።

በአማራ ክልል ከጎበኘኋቸው ዞኖች እስከአሁን ያልጎበኘሁት ዞን በመሆኑ ጉብኝቱን የተለየ ያደርገዋል።

የከሚሴ የኮሪደር ልማት ሥራ በጅምር ደረጃ ያለ ቢሆንም የ1.3 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ እና የእግረኛ መንገድ ሥራዎች የሚመሰገኑ ናቸው።

የኮሪደር ልማት ሥራ የሕዝባዊ ሥፍራዎችን ደረጃ ከፍ በማድረግ ዕሳቤ በሁሉም ደረጃ በመላው ኢትዮጵያ እየተተገበረ መሆኑን ያሳያሉ።

በከተማዋ ለሌማት ትሩፋት ሥራችን አስተዋጽዖ እያበረከተ ያለውን የኤልፎራ አግሮ-ኢንዱስትሪ የተቀናጀ የግብርና ልማት ፋብሪካንም ጎብኝተናል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top