ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ በጀት የተገነባው የህዝብ ፋርማሲ ተመረቀ

በደሴ ከተማ አስተዳድር ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ በጀት የተገነባው የህዝብ ፋርማሲ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

መድሃኒት ቤቱ በዝቅተኛ ዋጋ ለከተማው ማህበረሰብ የመድሃኒት አቅርቦት ከማቅረብ ባሻገር በቀጠናው ለሚገኙ አካባቢዎች በጅምላ ለማከፋፈል ታቅዶ በዘመናዊ መንገድ ተሰርቷል ተብሏል።

ለህብረተሰባችን ዋናው መሰረታዊ ነገር ላይ ትኩረት በማድረግ ህብረተሰቡ በመድሃኒት እጥረት የሚገጥመውን ችግር ለመቅረፍ በመንግስት፣ አልማ እና ማህበረሰብ የጋራ ቅንጅት ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

በከተማችን ከሚከናወኑ በርካታ የልማት እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ ለህብረተሰቡ ጥራት ያለውና በተመጣጣኝ ዋጋ የመድሃኒት አቅርቦት እንዲኖር የህዝብ ፋርማሲ በአምስቱም ክ/ከተማ የተሰሩት በቅርቡ በይፋ ስራ እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

ሁሉም የህዝብ ፍርማሲዎች በሙሉ አቅማቸው ወደስራ ሲገቡ የከተማዋ ነዋሪዎች በአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መልዕክት ተላልፏል።

በምርቃ ስነ ስረአቱ የአብክመ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱከሪም መንግስቱ፣ የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ ሳሙዔል ሞላልኝ፣ የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ አለማየሁን ጨምሮ የከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ ሌሎች አመራሮች ፣ የኃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top