የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

ደሴ የሠላም የልማትና የአገልግሎት አሰጣጥ ተምሳሌት እየሆነች ነው።

በዛሬው ዕለት የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን ለመፍታት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት፣ በደሴ ከተማ ግንባታው የተጠናቀቀውን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ህንጻ ስራን በይፋ አስጀምረናል።

መሶብ በተለያዩ ተቋማት በተበታተነ መንገድ ሲሰጡ የነበሩ አገልግሎቶችን ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት፣ የህዝቡን እንግልትና የቢሮክራሲ መጓተት ችግር በማስወገድ፣ ዜጎች ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ያስችላል።

ደሴ ከአብሮነትና ከፍቅር መናገሻነቷ ባለፈ ሠላምን በማስጠበቅ ልማትና በአገልግሎት ዝማኔ የጀመረችው ጉዞ የሚያስደንቅ ነው።

ደሴዎች ሰላም የልማት ውጤት መሆኑን በተግባር እያሳያችሁ በመሆኑ ይኸው የትብብር ትጋትና ውጤታችሁ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top