“የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ብቃት ያለው የጸጥታ ኃይል መገንባት ያስፈልጋል” ክቡር አረጋ ከበደ

“የጂኦ ስትራቴጂክ ጉዳይ የሀገራችንን ፖለቲካዊ ፍላጎት በምንፈልገው መልከዓ ምድር ላይ የምናስጠብቅበት መሣሪያ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና የሚኖራትን የኀይል ሚዛን ለማስጠበቅ፣ በቀጠናው ያላትን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ፍላጎቷን ለማሳካት በሕግ እና በጠንካራ ዲፕሎማሲ ላይ የተመሠረተ የወደብ እና ተፈጥሮ ሀብታችንን የመጠቀም መብታችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡

ለስኬቱም ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሰላም እና አንድነታቸውን ጠብቀው በጋራ መሥራት የሚገባቸዉ ሲሆን በተለይም ይህንን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ፣ ውስጣዊ ሰላምን ለማስፈን እንዲቻል ሥነ ምግባር ፣ ፍላጎት እና ብቃት ያለው የጸጥታ ኃይል መገንባት ያስፈልጋል”

ክቡር ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ለአማራ ክልል ፖሊስ አመራሮች የአቅም ግንባታ ሥልጠና መርሃ ግብር ላይ ካስተላለፉት መልእክት የተወሰደ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top