የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

መንግስት ለሰው ተኮር አጀንዳዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ለአካታች ልማት እየሰራ ነው።

በደሴ ከተማ የተመለከትናቸው የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርት ግብይት ማዕከል እንዲሁም የእንጀራ መጋገራሪያ አዳራሽ ስራዎች የሕዝባችንን የየዕለት ችግሮች ለመፍታት ለምናደርገው ጥረት ማሳያዎች ናቸው።

የግብይት ማዕከሉ ዋና ዓላማ አምራቾች እና ሸማቾችን በማገናኘት እና በመካከል ያለውን የተንዛዛ የግብይት ሰንሰለት በማሳጠር ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን ማረጋጋት ነው።

ማዕከሉ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን እና የእንስሳት ተዋጽኦዎች ግብይት ይካሄድባቸዋል።

የደሴ ከተማ የቧንቧ ውሃ የእንጀራ መጋገራሪያ አዳራሽ ግንባታ እንጀራ በመጋገር ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠርና ምርታማነትን በማስፋፋት የዜጎች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥን ዓላማ ያደረገ ነው።

የብልጽግና ጉዟችን ሁሉንም ማኅበረሰብ ተጠቃሚ በማድረግ ማኅበራዊ ፍትህን ያረጋገጠ ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ራዕይ የሚመራ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top