“ሴቶች መብትና ግዴታችን አውቀን ኃላፊነታችን መወጣት አለብን” የርዕሰ መስተዳድሩ ማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ፈንታዬ ጥበቡ (ዶ.ር)

(ታሕሳስ 24/2018 ዓ.ም) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት የሴት አመራሮች እና ሴት ሰራተኞች በሴቶች ማህበር አደረጃጀት ዙሪያ የጋራ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የአማራ ሴቶች ማህበር ምክትል ዳይሬክተር ወይዘሮ ሁላይሽ አወቀ የማህበሩን አሰራሮች እና አደረጃጀቶች እንዲሁም ማህበሩ የሚፈጽማቸውን ተግባራት በመወያያ ፅሑፍ ለውይይት ተሳታፊዎች አቅርቧል።

ዳይሬክተሯ አክለዉም ማህበሩ ከማንኛውም ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ነፃ የሆነና ለትርፍ ያልተቋቋመ በበጎ አድራጎት የሚሰራ መሆኑን አንስተዋል።

የክልላችን ሴቶች በተዛባ የስርአተ ፆታ አመለካከትና ጎጅ ልማዳዊ ግፊት ምክንያት ለዘመናት በልማት እኩል ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ሆነው መቆየታቸውን አብራርተዋል።

የክልሉ ሴቶች ማሕበር መንግስት ለመደራጀት በሰጠው እውቅና መሰረት ግንቦት 1990 ዓ.ም ፆታን መሰረት በማድግ የተመሰረተ አንጋፋ ማህበር ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ አባላት ይዞ ከክልል እስከ ታች ቀበሌ ድረስ ባሉት መዋቅሮች ከ42 ሺ በላይ የበጎ ፍቃድ አገልግሎ እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ማሕበሩ ሴቶች በአገራቸው ጉዳይ ላይ ከሩቅ ተመልካችነት ወጥተው እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ አላማ አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ ወይዘሮ ወይንሸት ዳኛቸው የሴቶች የሚደርስባቸውን ማሕበራዊ ጥቃት ለመከላከል ማሕበሩን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

በቀጣይም ማህበሩ የከፋ ችግር ላለባቸው እና ለአካል ጉዳተኞች ቅድሚያ በመስጠት ሰፊ ሥራ መስራት እንደሚጠበቅበት አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ገቢያ ተስፋ ጠንካራ አደረጃጀት እና መዋቅር መፍጠር ከቻልን በርካታ ዕንባ የሚያፈሱ ሴቶችን ችግር መፍታት እንችላለን ብለዋል፡፡

ስንደራጅ የሰላም አባሳደር እነሆናለን ያሉት ኃላፊዋ አደረጃጀቶችን በማጠናከር የሴቶች ቁልፍ ማሕበራዊ ችግሮ መፍቻች ማደረግ አለብን ነው ያሉት።

በተለያየ መንገድ ችግር ስለሚገጥማቸው ሴቶች የምንደርሰው ጠንካራ የሴቶች ማህበር አደረጃጀት ሲኖረን ነው ብለዋል፡፡

የርዕሰ መስተዳድሩ ማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ፈንታዬ ጥበቡ (ዶ.ር) የአማራ ሴቶች ማህበር እውነተኛ የሴቶች እንባ የሚጠረግበት

ተቋም ነው ብለዋል።

ማሕበሩ ሴቶ የሚደርስባቸውን ማሕበራዊ ችግር ለመቅረፍ ዳገት ቁልቁለት ወርዶ በርካታ ችግሮችን እየፈታ የሚገኝ ማህበር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አማካሪዋ አክለው ሴቶች ከተደራጀን ያሉብንን ክፍተቶች መሙላት፣ ችግሮች በጋራ መፍታት የምችል መሆናችን በተግባር ማሳየት አለብን ነው ያሉት።

መብትና ግዴታችን አውቀን በተገቢው መንገድ ኃላፊነታችን በመወጣት ችግር ለደረሰባቸው ሴቶች መብት መከበር በጋራ ባለቤት ሆነን መሥራት አለብን ብለዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top