“የበደልነውን ሕዝብ ለመካስ ዝግጁ ነን” የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ ታጣቂዎች

በምዕራብ ጎጃም ዞን በጃቢ ጠህናን ወረዳ በተሳሳተ መንገድ ታጥቀዉ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለዉ ገብተዋል።

ታጣቂዎቹ እንዳሉት፦ የአማራን ህዝብ ነጻ እናወጣለን በሚል በተሳሳተ መንገድ ጫካ በመግባት በህዝባችን ላይ የሰላም እጦት እንዲከሰት ምክንያት ሁነናል።

ከእንግዲህ የበደልነውን ህዝብ ለመካስና ለማገልገል ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል።

ሌሎች በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎችም የሰላም አማራጭን ተቀብለው እንዲገቡ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከጃቢ ጠህናን ወረዳ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top