ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ የመስኖ ልማትን ጎበኙ።

(ታኅሣሥ 15/2018 ዓ.ም) ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ የመስኖ ልማትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የሰሜን ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሰፋ ጥላሁን፣ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አዲሱ መሐመድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።

ሰሜን ሜጫ ወረዳ በቆጋ መስኖ ፕሮጀክት ተጠቃሚ የኾነ አካባቢ ነው።

አካባቢው በዓመት ተደጋጋሚ ጊዜ በማምረት በአትክልት፣ በፍራፍሬ እና በሌሎች ምርቶችም ይታወቃል።

ወረዳው በአማራ ክልል የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰባቸው አካባቢዎችም አንደኛው ነው።

አሁን ላይ በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም ተፈጥሯል። የወረዳው አርሶ አደሮችም በመደበኛ የልማት ሥራቸው ላይ ይገኛሉ።

ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በቆጋ መስኖ ልማት ፕሮጀክት እየለማ የሚገኝ የአትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም ለበጋ መስኖ ልማት የተዘጋጀን ማሳ ነው የጎበኙት።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top