(ታኅሣሥ 08/2018 ዓ.ም) ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የቡሬ ወለጋ የመንገድ ፕሮጄክት የሥራ አፈጻጸም ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር)፣ የምዕራብ ጎጃም ዞን አሥተዳዳሪ እድሜዓለም አንተነህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የቡሬ ወለጋ የመንገድ ፕሮጄክት የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎችን የሚያስተሳስር በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ትልቅ ፋይዳ ያለው ነው።
ትርፍ አምራች የኾነውን አካባቢ በማስተሳሰር ግንኙነቱን በማጠናከር ለአካባቢው እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት የመንገድ ፕሮጄክት ነው።
የዓመታት የሕዝብ ጥያቄ የነበረው የመንገድ ፕሮጄክቱ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲኾን ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግበት ተመላክቷል ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።

