የሰላም ስምምነት ተከትሎ በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በጫካ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም አማራጭ ተቀብለዋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት( አፋሕድ) መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በጫካ የነበሩ ታጣቂዎች ገብተዋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት( አፋሕድ) መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከፍተኛ አመራሮች የመንግስትን የሰላም አማራጭ ተቀብለዋል።
የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ የኔዋ ደመቀ የመንግስትን የሰላም አማራጭ ለተቀበሉ አካላት አቀባበል ያደረጉ ሲሆን የሰላም አመራጩን የተቀበሉ አካላት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት( አፋሕድ) መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ እንደገቡ ገልጸዋል።
በመጨረሻም የህዝባችሁን ስቃይና እንግልት በመረዳት እና ኢትዬጵያን ለማፈራረስ ከሚሰሩ የታሪካዊ ጠላቶቻችንን ሴራ በመረዳት እና በመገንዘብ ለሰላም ትርጉም በመስጠት አስቀድማችሁ መምጣታችሁ ለህዝባችሁና ለሀገራችሁ ያላችሁን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለው በቀጣይ የበደላችሁትን ህዝብ ለመካስ ምቹ እድል ስላገኛችሁ ህዝባችሁን ይቅርታ በመጠየቅ ስለ ሰላም ዘወትር ልትዘመሩ ይገባል።
በማለት በቀጣይ የህዝባችን ሰላም እንዲረጋገጥ ከመንግስት ጎን ሆነው እንዲሰሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።
እጃቸውን በሰላም የሰጡ ታጣቂዎችም በበኩላቸው በቀጣይ በጦርነት የባከነውን ጊዜ በልማት ለማካካስ ከመንግስት ጎን በመሆን ህዝባቸውን ለመካስ ቀን ከሌት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

