(ታሕሳስ 7/2018 ዓ.ም) በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በማዕከላዊ ዞን የአስተዳድር ክላስተር ብልጽግና ፓርቲ ሕብረት አንድ “በመደመር መንግሥት እይታ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ ሐሳብ ለሕብረቱ አባላት ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
በስልጠናው በሕብቱ ስር የሚገኙ የሁሉም ተቋማት አመራሮችና ሁሉም የሕብረቱ አባላት ተሳታፊ ናቸው።
በመደመር መንግስት ዕይታ፤ የግብርና እና የገጠር ትራንስፎርሜሽን እንዲሁም የኢንዱስትሪ ዘርፍ እምርታላይ ትኩረት ያደረገ ገልጻ ለአባላት ቀርቦ ወይይት እየተደረገበት ይገኛል።
ለሕብረቱ አባላት የሚሰጠው ስልጠና ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

