መገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ያረፈበት ቦታ 870 ሄክታር መሬት ይሸፍናል። የመስኖ ልማት ፕሮጀክቱ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ 17 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በመስኖ የማልማት አቅም አለው።
ግድቡ ሲጠናቀቅ 185 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የውኃ መጠን የመያዝ አቅም ይኖረዋል።
ከሚይዘው የውኃ መጠን ውስጥ 32 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የሚሆነው ለንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት የሚውል ይሆናል።
መገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቱ ከ45 ሺህ በላይ አባዎራዎችን የመስኖ ልማት ተጠቃሚ ያደርጋል።
በዓመት ሦስት ጊዜ እንዲያመርቱ በማድረግ ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ እንዲያሻሸሉ እድል ይፈጥራል።
ፕሮጀክቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ወደ ስራ እንዲገባ ከቀን የስራ ሰዓት በተጨማሪ ሌሊትን ጨምሮ እየተሠራ ይገኛል።

