ሰላምን ለማረጋገጥ ችግሮች ላይ መወያየት፣ መግባባት እና የጋራ መፍትሔ ማስቀመጥ ይገባል።

(ታኅሣሥ 02/2018 ዓ.ም) ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በምዕራብ ጎጃም ዞን ከቋሪት ወረዳ ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው።

በውይይቱ ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አሥተባባሪ አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር)፣ የምዕራብ ጎጃም ዞን አሥተዳዳሪ እድሜዓለም አንተነህ፣ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ ረጋሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን አሥተዳዳሪ እድሜዓለም አንተነህ የቋሪት ወረዳ ሕዝብ ሰላምን በመጠበቅ እና እንግዳ በመቀበል የታወቀ ነው ብለዋል። ባለፉት ዓመታት ግን የሰላም እጦት ገጥሞት መቆየቱን ተናግረዋል።

ሰላም ወዳዱ የቋሪት ሕዝብ ሰላም እንዲመለስ እና ልማት እንዲረጋገጥ መምከር እና የጋራ መፍትሔ ማስቀመጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) በአማራ ክልል የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ልጆቻችን እንዳይማሩ፣ ነጋዴዎች እንዳይነግዱ፣ አርሶ አደሮች እንዳያለሙ አድርጎ ቆይቷል ብለዋል።

ባለፉት ጊዜያት የገጠመው የጸጥታ ችግር የባሕል እና የእሴት መሸርሸር እንዲፈጠር አድርጓል ነው ያሉት።

የተፈጠረው የእሴት መሸርሸር ችግር ለነገም ዳፋው ከባድ እና ሕዝብን የሚገዳ መኾኑን ተናግረዋል።

ቋሪት እና አካባቢው ረዘም ላለ ጊዜ በችግር ውስጥ መቆየቱን ገልጸዋል።

ሰላምን ለማረጋገጥ ችግሮች ላይ መወያየት፣ መግባባት እና የጋራ መፍትሔ ማስቀመጥ ይገባል ነው ያሉት ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top