የደብረ ብርሃን – ደነባ – ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር – ደነባ የመንገድ ግንባታ በተሻለ አፈፃፀም ላይ ነው

(ታህሳስ 1/2018 ዓ.ም) :- 108.26 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የደብረ ብርሃን – ደነባ – ለሚ መገንጠያ እና ጅሁር – ደነባ የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ ሥራ በተሻለ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የመንገድ ግንባታ ሥራው ሁለት ክፍሎች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው የደብረብርሃን – ደነባ – ለሚ መገንጠያ የመንገድ ክፍል 69.85 ኪሎሜትር እንዲሁም የጅሁር – ደነባ ሁለተኛው የመንገድ ክፍል 38.41 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡

በእስካሁኑ የፕሮጀክቱ የግንባታ እንቅስቃሴ የአፈር ሙሌት ፣የቆረጣ ፣አነስተኛ ድልድይና የቱቦ ቀበራ፣ የካፒንግ፣ የሰቤዝ ንጣፍ፣ የቤዝ ኮርስና የአስፓልት ጠጠር መፍጨት፣ የቤዝኮርስ እንዲሁም ከ16.77 ኪሎ ሜትር በላይ የአስፋልት ኮንክሪት ንጣፍ ለማከናወን ተችሏል፡፡

ግንባታውን የሚያካሂደው የሥራ ተቋራጭ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.ግ.ማህበር ሲሆን የማማከርና የቁጥጥሩን ሥራ ኤቢኤም ኢንጂነርስ እና ፕላስ ኮንሰልት ኃ.የተ.ግ.ማህበር (ንዑስ ኮንሰልታንት) በመሆን እያከናወኑት ይገኛል፡፡

ለመንገዱ ግንባታ የሚውለው 3,613,766,908.69 (ሶስት ቢሊዮን ስድስት መቶ አስራ ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ስልሳ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስምንት) ብር በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መንግስት የተሸፈነ ነው፡፡

መንገዱ በዞን 25.5 – 35.5 ሜትር ፣በወረዳ 21.5 ሜትር ፣በቀበሌ 12 ሜትር እንዲሁም በገጠር ከ 10- 11 ሜትር አጠቃላይ የጎን ስፋት አለው፡፡

የመንገድ ሥራው ሲጠናቀቅ የአካባቢው ማህበረሰብ የትምህርት፣ ጤና እና መሰል ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግልጋሎቶችን በአፋጣኝ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው፡፡

ከዚሁም ባሻገር በሃገሪቱ ትልቁ የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ የደብረብርሃን ኢንዱስትሪያል ፓርክ እና ሌሎች በደብረብርሃን ሪጂዮ-ፖሊታን ከተማ አካባቢ የሚገኙ የማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካዎች እና ኢንዱስትሪዎች ጥሬ ዕቃዎቻቸውንና የተለያዩ ምርቶቻቸውን ለማጓጓዝ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

በተጨማሪም ከሙከጡሪ – አዲስ አበባ – ደብረብርሃን እንዲሁም ወደ አዋሽ አርባ – ጂቡቲ ለሚጓዙ የመንገድ ተጠቃሚዎች አማራጭ መስመር በመሆን ያገለግላል መሆኑን ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top