የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ከኮምቦልቻ ከተማ ወጣቶች ጋር እየተወያዩ ነው።

(ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም) በመድረኩ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የከተማዋ ወጣቶች ተገኝተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በአካባቢያቸው ዘላቂ ሰላም በሚሰፍንበት ኹኔታ እየመከሩ ነው።

በተጨማሪም የተለያዩ የልማትና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን እያቀረቡ ነው።

በመድረኩ በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በፓርቲው የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍሰሀ ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top