(ታኅሣሥ 01/2018 ዓ.ም) በሰሜን ጎንደር ዞን የተለያዩ ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች ላይ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የክልል እና የመከላከያ ሠራዊት የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት እየተጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ መልዕክት ያስተላለፉት በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች ዘላቂ ሰላምን ለማጽናት የሚያስችሉ የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች እየተካሄዱ ነው ብለዋል።
የክልሉ መንግሥት ከምንጊዜውም በላይ ለዘላቂ ሰላም እና ልማት መረጋገጥ ቁርጠኛ ኾኖ እየሠራ እንደኾነም ተናግረዋል።
“ለሰላም ትክክለኛው ጊዜ ትናንት ነበር፤ ትናንት አልፏል፤ ይሁንና ዛሬም አልረፈደም” ብለዋል። ለሰላም ረፍዶ የሚያውቅበት ጊዜ የለም ነው ያሉት።
በጫካ ትግል ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ኃይሎች እየወሰዱት የሚገኘው የሰላም አማራጭ ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ብለዋል።
በየአካባቢው እየተሠሩ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ማኅበረሰቡ የሰላም ባለቤት ኾኖ መጠበቅ እና በዘላቂነት ማጽናት እንደሚገባም አንስተዋል።
የሰላም አማራጭን መከተል እና ለሰላም ቁርጠኛ ኾኖ መሥራት ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርግ የመፍትሔ አቅጣጫ ነው ብለዋል።
መንግሥት የማኅበረሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ድጋፍ እያደረገ እና በቁርጠኝነት እየሠራ ነው ያሉት ዶክተር ዘሪሁን ማኅበረሰቡም ድጋፉን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook https://www.facebook.com/share/1ZfJoPFYV7/
Ticktock https://www.tiktok.com/@amhara.region.pre?_r=1…
Telegram https://t.me/ANRS_PresidentOffice
Twitter https://x.com/AmGovernoffice/header_photo
You Tube https://www.youtube.com/@amhararegionpresidentoffic1192
WhatsApp https://whatsapp.com/channel/0029Vb6ZZXk1t90V1p2qyV03

