“በቴክኖሎጅው ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለማፍራት እሰራን ነው” ስቡህ ገበያው (ዶ/ር)

የአማራ ክልል ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ከርዕሰ መስተዳደር ጽሕፈት ቤት ዲሊቨሪ የኒት ጋር በመተባበር የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡

የክልላችን መንግስት በክልሉ ተስተካካይ የኢኮኖሚ ልማት ለማረጋገጥ ከሀገር አቅፍ የኢኒሼቲቮች በተጨማሪ 7 የኢንሼቲቪ ፕሮግራሞች በመለየት በትኩረት ይዞ እየሰራ ይገኛል፡፡

በክልሉ ከሚተገበሩ ኢኒሼቲቮች መካከል ዲጅታል አማራ አንዱ ሲሆን “ዲጂታል ክህሎት ለሥራ ፈጠራና ሙያ ልማት” በሚል መሪ ሐሳብ የአስልጣኞች ስልጠና በዛሬው እለት መሰጠት ጀመሯል፡፡

የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ዴሊቨሪ ዩኒት አስተባባሪ አቶ ሞገስ ተኬ በስልጠናው 60 የሥራ እና ክህሎት ቢሮ ሰራተኞች እንዲሁም 40 አስልጣኝ መምህራን እና የኮሌጅ ዲኖች ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አቶ ሞገስ እንደገለፁት፦ የዲጂታል ማርኬቲንግ ፤ ኔትወርክ ኮንቪገሬሽን እና ሜንቴናንስ ፤ ግራቪክ ዲዛይን ፤ ዌብ ዲቨሎፕመንት ፤ ኮንቴንት ክሬሽንና ሌሎች የቴክኖሎጂ ሙያዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ነው ብለዋል።

የክልሉ መንግስት በዲጂታል ክህሎት ብቁና ተወዳዳሪ ወጣቶችን ለማፍራት የአጭር ጊዜ የሙያዎች ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በስልጠና ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሥራ እና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ ስቡህ ገቢያው (ዶ/ር) የዲጂታል ክህሎት ስልጠናው የዓለምን ሁኔታ በመገንዘብ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ተወዳዳሪና ተሳታፊ የሚሆኑ ወጣቶችን ለመፍጠር የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

በክልሉ በሚገኙ ከተሞች ስልጠናውን ተደራሽ በማድረግ 5 ሚሊዮን ወጣቶችን በማሰልጠን በዘርፉ ጉልህ ሚና እንዲጫወት ቢሯቸው አቅዶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ወጣቶችን በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ላይ ያላቸውን የመወዳደር አቅም ከፍ በማድረግ 120 ሺህ ዜጎችን በዲጅታል ክህሎት ብቁ በማድረግ ሥራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ኃላፊው አክለውም በቴክኖሎጅው ዘርፍ በቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት ሀገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ዳር ለማድረስ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በክልሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ ሂደት ውስጥ የላቀ ተሳትፎ ያላቸውን ዜጎች ለማብቃት የስራና ክህሎት ቢሮ እንደሚተጋ ተናግረዋል፡፡

“ዲጂታል ክህሎት ለሥራ ፈጠራና ሙያ ልማት” በሚል መሪ ሐሳብ የሚሰጠው ስልጠና ዛሬን ጨምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top