በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል የዘላቂ ሰላም ስምምነት ተደርጓል።
ስምምነቱ የክልሉ መንግሥት ለሰላም የሰጠው አማራጭ አንዱ አካል የኾነ እና ለቀጣይ የሕዝብ ሰላማዊ እፎይታ መሠረት የሚጥል ነው ተብሏል።
በሁለቱ ወገኖች ስምምነት በአደራዳሪነት የአፍሪካ ኅብረት እና ኢጋድ ተሳትፈዋል።
የሰላም ስምምነቱ በአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ተወካይ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ መካከል ተደርጓል።
በስምምነት ሥነ ስርዓቱ ላይ ከጦርነት ያተረፈም ኾነ በጦርነት የተጠናቀቀ ግጭት ባለመኖሩ ይህ ድርድር ለክልሉ ሕዝብ ሰላም መነሻ እና ለሰላም የተሰጠ ተግባር ነው።

