በምዕራብ ጉጂ ዞን የሚገኘው ኮር የሠላምና የልማት ወይይት አካሄደ፡፡

(ኀዳር 04 ቀን 2018 ዓ.ም) የደቡብ ዕዝ ኮር በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ጉጂ ዞን እንዲሁም በዙሪያው ያለውን አካባቢ የሠላምና ፀጥታ ደህንነት ለማስቀጠል የሚያስችል ውይይት አካሂዷል።

የውይይቱ የትኩረት አቅጣጫ በሁሉም አካባቢዎች የሸኔ ሃይሎችን መከላከል በጥንቃቄ መለየትና ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ግጭቶች እንዳይከሰቱ ከአገር ሽማግሌዎችና ከሐይማኖት አባቶች እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት መስራት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ መሆኑ ተገለሰጿል።

ውይይቱን የመሩት የደቡብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጄር ጀኔራል ደስታ ተመስገን በቀጠናው በመገኘት የሠላምና ልማት የፀጥታ ሃይሎች ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅተው እና ተናበው መስራት እንደሚገባቸው የገለፁ ሲሆን የፀጥታ አካላት ህብረተሰቡን ያሳተፈ የሰላም ማስከበር ስራዎችን አጠናክረው መቀጠል ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል፡፡

አሁን እየመጣ ያለው አንፃራዊ ሰላምም እንዲሁም ሃገራዊ እድገት እንዲቀጥል በየጫካው ያለው ሁሉም ታጣቂ ኃይል በሰላም እንዲገባ ሐይማኖት አባቶች አባገዳዎች የሃገር ሽማግሌዎች ሊሰሩ ይገባልም ሲሉ ጄኔራል መኮነኑ አሳስበዋል፡፡

በቀጠናው የሚገኘው ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጄነራል ሁሴን አህመድ የኮሩ ሠራዊት ቀን ሳይል ማታ በርካታ የሠላምና የልማት ስራዎችን ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ተናቦ እየሠራ መሆኑን ገልፀው ተዘግተው የነበሩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ስራ መጀመራቸውን ተናግረዋል ሲል የዘገበው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top