የሀገራችን ኢኮኖሚ እድገት መሠረቱ የግብርናው ዘርፍ ነው። ይሕ በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኝ የስንዴ ሰብል ነው።
የግብርናው ምርታማነት እደገት ለሌሎች ዘርፎች እደገት ወሳኝ ነው። ዘመናዊ የእርሻ ቴክኖሎጂዎችንና የግብአት አማራጮችን በመጠቀም የዘርፉን ውጤታማነት በተፈለገው ደረጃ ማሳደግ ይኖርብናል።
የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት በተፈለገው ደረጃ ማሳደግ ከተቻ ደግሞ የአቅርቦት ዋስትናን ከማረጋገጥ በተጨማሪ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ የምንችልበት ነው።
ለዘርፍ እድገት የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ የሚጠይቅ ቢሆንም በግብርና ሙያ ላይ የተሰማሩ መለያዎች ዋነኛ ተዋናኞች ናቸው።
በዘርፉ የተሰማራው አርሶ አደር ምርታማነትን የሚጨምሩ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን እንዲጠቀም ለማድረግ የማይተካ ሚና አላቸው።
መንግሥት ግብርና ለእድገትና ብልጽግና ያለውን እምቅ አቅም መሠረት በማድረግ ለዘርፉ ቅድሚያ በመስጠት በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። ዘርፉን ማዘመንና ማሳደግ ደግሞ ጤናማ የሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲኖር የሚያደርግ ነው።
ባለፉት ዓመታት የእርሻ መካናይዜሽን ለማስፋፋት በተደረገው ጥረት ምርታማነት ከመጨመር ባለፈ ለበርካታ የገጠር ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የሚያስችሉ ስራዎች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው።
ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ አዳዲስ የአመራረት ዘዴዎችና የቴክኖሎጂ አማራጮች በአርሶ አደሩ ዘንድ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛል።
ለግብርና የተመቸ ብዝሃ ጸጋ ባለቤቶች ነን። ያለንን እምቅ ፀጋ በአግባቡ በማልማት ኢኮኖሚያዊ እድገታችን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
ግብርና የኢኮኖሚ እድገት ዋስትና!

