(ጥቅምት 28፣ 2018) የመገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ 870 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ÷ ሥራው ሲጠናቀቅ 17 ሺህ ሔክታር በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ቀሪ ሥራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።
የመገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀክት በሚጠናቀቅበት ወቅት የአካባቢውን የግብርና ምርታማነት የሚያሳድግ ይሆናል ሲሉም አመልክተዋል፡፡

