ያላግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መኾኑ ተገለፀ።

(ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም) የመንግስት ሰራተኛውን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የተደረገውን የደመወዝ ጭማሪ ተከትሎ ያላግባብ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

የባሕርዳር ከተማ አስተዳድር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኀላፊ አቶ አደራ ጋሻ በመግለጫቸው የደመወዝ ጭማሪን ተከትሎ የተደረገ የዋጋ ማሻሻያ አለመኖሩን ገልፀው ያላግባብ ተነጋግሮ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 221 ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።

መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ አንዳንድ ስግብግብ ነጋዴዎች 121 የንግድ ድርጁቶች ፣ 8 ስቶሮችንና ምርት ደብቀው በተገኙት ላይ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ግብረ ሃይሉ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል ብለዋል።

የደመወዝ ጭማሪን ተከትሎ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ መንግስትና መንግስት ሰራተኛውን ለማለያየት የሚደረግ በመኾኑ በትኩረት የሚሰራ ነው ብለዋል።

የምርት እጥረት እንዳይከሰት በሸማች ማህበር ምርት እንዲሰራጭ እየተደረገ ሲኾን ነጋዴዎች ምርት ከመደመቅ እንዲቆጠቡና ኗሪው ያላግባብ የሚጨምሮ ነጋዴዎችን እንዲያጋልጡ አሳስበዋል ።

ከህግ አግባብ መግለጫ የሰጡት የባሕርዳር ከተማ አስተዳድር ፍትህ ጽ/ቤት ዋና ኀላፊ አማርከኝ ዬሴፍ የደመወዝ ጭማሪን ተከትሎ የተከሰተውን ያላግባብ የዋጋ ጭማሪ ከህግ አግባብ ተገቢ አለመኾኑን ገልፀዋል።

ነጋዴው በንግድ ድርጁቱ የምርት ዋጋ ዝርዝር በሚታይ ቦታ በመለጠፍ ገዥው የተሻለውን አይቶ እንዲገዛ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ኀላፊው አያይዘው ነጋዴው በህብረት ተነጋግር ዋጋ መጨመርና የንግድ እቃ መደበቀ በህግ እንደሚያስቀጣ አውቆ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top