ኢትዮጵያ ውስጥ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ወጣቶች በነጻ የኮዲንግ ስልጠና መውሰዳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዲጂታላይዜሽንን በሚመለከት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሸና ማብራሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ወጣቶች በነጻ የኮዲንግ ስልጠና ወስደዋል ብለዋል።
ይህ ትልቅ ቁጥር መሆኑን ጠቁመው 93 ሚሊዮን ደንበኞች ደግሞ የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ ሲሆኑ 55 ሚሊዮን ዜጎች የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ሲሉም ገልጸዋል።
ይህ ኢትዮጵያን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የጀመረነው ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን አመላካች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናግረዋል።

