ባሕርዳር – ጢስ እሳት አስፓልት መንገድ ፕሮጀክት

(ጥቅምት 15፣ 2018) የጢስ ዓባይ ፏፏቴ መዳረሻ የኾነው የባሕርዳር – ጢስ እሳት መንገድ ግንባታ አፈጻጸም ለማሻሻል እየተሠራ ነው።

የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቱ የግንባታ ሒደት 48 ነጥብ 33 የደረሰ ሲሆን፣ አስፋልት ለማንጠፍ የሚያስችሉ የቤዝኮርስ ጠጠር ማምረት እንዲሁም የውኃ መፋሰሻ ግንባታ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው።

የመንገድ ፕሮጀክቱ 21 ነጥብ 2 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲኾን፣ ሀገር በቀሉ መልኮን ኮንስትራክሽን በማከናወን ላይ ይገኛል።

ጎንድዋና ኢንጅነሪንግ የማማከር እና የቁጥጥር ሥራውን ያከናውናል።

ለመንገድ ግንባታው 975 ሚሊዮን ብር በፌደራል መንግስት በጀት ተይዞለታል።

የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ ወደ ጢስ ዓባይ ፏፋቴ ለሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።

በአካባቢው የሚመረቱ የተለያዩ የግብርና ምርቶች በቀላሉ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማድረስ ያስችላል።

ወደ ባሕርዳር ከተማ የሚደረገውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ያሳልጣል።

በአጠቃላይ በዚህ ዓመት የባሕርዳር – ጢስ እሳት አስፓልት መንገድ ፕሮጀክት አፈጻጸም እስከ 80 በመቶ ለማድረስ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top