(ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም) ከጥቅምት 14/2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው የጣና ፎረም በዋዜማው ወደ ውቢቷ ባሕር ዳር የገቡ አፍሪካውያን መሪዎች ምሽታቸውን በጣና ሐይቅ ዳርቻ እያሳለፉ ነው።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎችም የከተማ አሥተዳደሩ እና የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች በባሕር ዳር ከተማ ደጅአዝማች በላይ ዘለቀ አየር ማረፊያ ተገኝተው እንግዶቹን ከተቀበሉ በኃላ የጣና ሐይቅ ዳርቻ መዝናኛዎች ላይ ከእንግዶቻቸው ጋር እያሳለፉ ይገኛሉ።
ባማረው የጣና ሐይቅ ዳርቻ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች አፍሪካዊ ለዛ ያላቸውን የጥበብ ሥራዎች ለእንግዶች እያቀረቡ ነው።

