አፍሪካውያን መሪዎች እና ምሁራን ለጣና ፎረም ዝግጅት ወደ ባሕር ዳር እየገቡ ነው።

(ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም) ጣና ፎረም በአፍሪካ የደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ የአሕጉሪቷ መሪዎች እና ምሁራን የታላቁ የጣና ሐይቅ መገኛ በኾነው ባሕር ዳር ከተማ ከትመው የሚወያዩበት ከፍተኛ ፎረም ነው።

ፎረሙ ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም ጀምሮ 11ኛ ፎረሙን በባሕር ዳር እና አዲስ አበባ ከተማ ያካሂዳል።

ባለዘንባባዋ ከተማም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በመግባት ላይ የሚገኙ እንግዶቿን ከዋዜማው ጀምራ እየተቀበለች ነው።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች በባሕርዳር ደጅአዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው እንግዶችን እየተቀበሉ ይገኛሉ።

የአፍሪካውያን እንግዶች የባሕር ዳር ከተማ ቆይታ ያማረ ይኾን ዘንድ አሥፈላጊው ዝግጅት እንደተደረገም ታውቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top