መስከረም 27/2017 ዓ.ም) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት አመራሮችና ሰራተኞች “ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር!” በሚል መሪ ሐሳብ ውይይት አካሂደዋል፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደሳለኝ የብሔራዊ ጥቅም ፈተናዎች እና መፍትሔዎችን የሚዳስስ የመወያያ ጽሑፍ ለውይይቱ ተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡
እንደ ሀገር ኢኮኖሚያዊ አቅማችን ለማጠናከር ዲፕሎማሲ አቅም መገንባትና ብሔራዊ ጥቅማችንን ሚያረጋግጥ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል፡፡
ብሔራዊ ጥቅም በመንግስት ብቻ የሚከበር ስላልሆነ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶችን በማወቅ የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
የባሕር በር ያስፈልገናል ስንል ምክንያታዊ ሆነን ነው ያሉት ጽሕፈት ኃላፊው ለአለም አቀፍ ማህበረሰህ ታሪካዊ እውነታውና ፍትሀዊነቱን ማስረዳት አለብን ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም የኢትዮጵያን የባሕር ብር ጉዳይ እውነታውን ለማስጨበጥ ቀጣይነት ያለው የተቀናጀ የዲፕሎማሲ ስራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ስኬቶቻችንን ለአለም በተገቢው መንገድ ማስረዳት፣ የጠላቶቻችን ዘመቻ መመከት የቀደመ ስህተቶችን የሚያርም የተግባቦት ስራ መስራት አለብን ብለዋል፡፡
የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች የቀረበውን የመወያያ ጽሑፍ መሠረት በማድረግ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ የሁላችንም ኃላፊነት በመሆኑ በጋራ ትግል ማድረግ ይኖርብናል ሲሉ ሐሳብና አስተያየትአንስተዋል።
የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብደላ ኑሩ የባሕር በር ጉዳይ የቅንጦት ሳይሆን የኢኮኖሚ ጉዳይ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ብለዋል።
መንግስት እያከናወናቸው ለሚገኙ ስራዎች ድጋፍ በመስጠት ወደባችን በሰላም እና በድርድር ማስመለስ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ደሳለኝ በሰጡት ማጠቃለያ የብሔራዊ ጥቅማችን ዋነኛ ሳንካ የሆነውን የውስጥ ሰላማችን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ድህነትና ኋላቀርነትን ለማስወገድ ኢኮኖሚያችን ላይ ተግተን መስራት ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም ብለዋል።
