ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የወልድያ ከተማን የኮሪደር ልማት ጎበኙ።

(መስከረም 23/2018 ዓ.ም) የአማራ ክልል፣ የሰሜን ወሎ ዞን እና የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የወልድያ ከተማን የኮሪደር ልማት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ላይ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ እና የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሃ ደሳለኝን ጨምሮ የወልድያ ከተማ እና የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top