በአማራ ክልል 3 ነጥብ 48 ሚሊዮን ተማሪዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው

በአማራ ክልል በአሉ ሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ ክስተቶች ምክንያት በትምህርት ዘርፉ እየደረሰ ያለውን ችግር ለመፍታት ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው።

ለውይይት መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)፤ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በክልሉ 3 ነጥብ 48 ሚሊዮን ተማሪዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ መሆኑን ተናግረዋል።

በትምህርት ዘመኑ 7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ ሲሠራ መቆየቱን ያነሱት መነሻ ጽሁፍ አቅራቢው፤ የተመዘገቡት ተማሪዎች መጠን የቅዱን 47 በመቶ ብቻ መሆኑን አብራርተዋል።

በትምህርት ዘመኑ 3 ነጥብ 48 ሚሊዮን ተማሪዎች ተመዝግበው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ቢሆንም፤ 3 ነጥብ 96 ሚሊዮን ተማሪዎች አልተመዘገቡም ሲሉ ተናግረዋል።

ተማሪዎች ተመዝግበው ትምህርት ባለመጀመራቸው ለተለያዩ ማኅበራዊ ችግሮች እየተዳረጉ ነው ብለዋል።

ህፃናት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት እያመለጣቸው ነውም ሲሉ ገልጸዋል ሲል የዘገበው ኢ.ፕ.ድ. ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top