የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ በሚቀርቡ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ መከረ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ በሚቀርቡ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ መከረ

*****************

በፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ፤ ምክር ቤቱ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ለሚያካሂደው 6ኛ የፓርላማ ዘመን 4ኛ የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ቀርበው በሚፀድቁ የውሳኔ ሃሳቦች ላይ መክሯል።

የቋሚ ኮሚቴውን ውይይት የመሩት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፤ ቋሚ ኮሚቴው በ2017 በጀት ዓመት የሚያከናውናቸው ዝርዝር ተግባራት የተካተቱበት እቅድ እንዲቀርብ ጠይቀው፤ የቋሚ ኮሚቴው ፀሐፊ አቶ ኃይሉ ኢፋ አቅርበው ሰፊ ወይይት ተደርጎበታል።

አቶ ሽመልስ በቋሚ ኮሚቴው አባላት የተሰጡ ግብዓቶች ጠቃሚ በመሆናቸው ለምክር ቤቱ በሚቀርበው የቋሚ ኮሚቴው የውሳኔ ሃሳብ ላይ እንዲካተት ማሳሰባቸው ተገልጿል።

የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ያለፈውን የቋሚ ኮሚቴውን ቃለ ጉባኤ መርምሮ በማፅደቅ ውይይቱን ማጠናቀቁን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል ኢ ቢ ሲ ዘግቧል።

+6

All reactions:

1212

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top