የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የባለድርሻ አካላት ውይይት በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።
(ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም) በአማራ ክልል የከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የባለድርሻ አካላት ውይይት በባሕር ዳር ተጀምሯል።
በውይይቱ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አህመዲን መሐመድን (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና የዘርፉ አጋር አካላት ተገኝተዋል።
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ቁጥጥር እና ትግበራ፤ አጠቃላይ የፕሮጀክት አፈጻጸም ግምገማ እና በፕሮጀክት አተገባበር ሂደት ላይ የሚስተዋሉ የአፈጻጸም ጉድለቶች የውይይቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች ናቸው ተብሏል።
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ያሉባቸውን ችግሮች በመፍታት አፈጻጸማቸውን በሚያሻሽሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።