በእብናት ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።

(ታኅሣሥ 26/2018 ዓ.ም) በደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።

ታጣቂዎቹ የበደልነውን ሕዝብ ለመካስ እና ለማገልገል የሰላምን አማራጭ ተቀብለናል ብለዋል።

የእብናት ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኀላፊ ጸዳል ካሳ ታጣቂዎቹ የቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው መግባታቸው ለሰላም ያላቸውን ዋጋ የሚያሳይ እና ሕዝባቸው የሰላም አየር እንዲያገኝ የተረዱ መኾናቸውን የሚያመላክት መኾኑን ገልጸዋል።

ወንድም ከወንድሙ ጋር የሚደረግ መገዳደል ለሀገርም ኾነ ለሕዝብ የማይጠቅም መኾኑን ተናግረዋል።

ከእብናት ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሌሎች ታጣቂዎችም የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top