“ደም መለገስ የሰብአዊነት መግለጫ ነው” የርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት አመራርና ሰራተኞች

(ታሕሳስ 24/2018 ዓ.ም) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት አመራር እና ሰራተኞች ደም ለገሱ።

አመራርና ሰራተኞቹ “ደም መለገስ የሰብአዊነት መግለጫ ነው” በሚል መሪ መልዕክት ነው ለባሕርዳር ደም ባንክ አገልግሎት ደም የለገሱት።

ደም በመለገስ ውድ የሆነውን የሰውን ልጅ ህይወት ከመታደግ በላይ የሚያስደስት ተግባር እንደሌለ ደም ለጋሾች ገልጸዋል።

በደም እጥረት ምክኒያት መዳን እየቻሉ ችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን ሕይወት መታደግ ሰብአዊ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

አቅምና ሁነታው የሚፈቅድለት ሁሉ ደም በመለገሰ ለወገን ደራሽነቱን ማሳየት አለበት ያሉት ደም ለጋሾች በቀጣይም በበጎ ፈቃደኝነት ደም እንደሚለግሱ ቃል ገብተዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top