በፅንፈኛ ቡድኑ ተቀብሮ የነበረ ተተኳሽ እና የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ።

በኤፍራታና ግድም ወረዳ በፅንፈኛ ቡድኑ ተቀብሮ የነበረ ተተኳሽ እና የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኤፍራታና ግድም ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ገለፀ።

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ አላላ ቀበሌ በህብረተሰቡ ጥቆማ እና በመንግስት የጸጥታ ሀይል ክትትል ፅንፈኛው ቀብሮት የነበረው ተተኳሽ እና የጦር መሳርያ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኤፍራታና ግድም ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ካሳ ገልጸዋል።

ፅንፈኛው በየ ሜዳው፣ በየ አጥር ስር እና ጥሻ ውስጥ ቀብሮት የነበረው ተተኳሽ እና የጦር መሳርያ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ውሏል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ ብትን ተተኳሽ የዲሽቃ ጥይት 730፣ በሳጥን (6)ሳጥን የድሺቃ ጥይት ፣

በድምሩ 1ሺህ 1መቶ 55 የድሽቃ ጥይት፣ 1:ፋል መሳርያ፣ 1ጁም three መሳርያ፣ 3 ኤስ ኪዬስ ክላሽ ፣ 1ባለ ሰደፍ ክላሽ ፣4 ምንቶፍ፣ 1በልጅግ ፣2ምንሽር ፣1የብሬን አፈ ሙዝ በድምሩ 14የጦር መሳርያ እና 1ሺህ 155 ተተኳሽ በመሬት ውስጥ ተቀብሮ መገኛቱን ተናግረዋል።

በመጨረሻም ሀላፊው የአከባቢው ህዝብ ከመንግስት ጎን ያለውን ደጀንነቱን በማስቀጠል በልማት ተጠቃሚነቱን እና ሰላሙን ማረጋገጥ እንዳለበት ማሳሰባቸውን ከኤፍራታና ግድም ወረዳ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top