የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

በአረንጓዴ የብልጽግና ጉዞ ለትውልዱ ምቹ ሀገር የማስረከብ ጉዟችን በሁሉም መስክ በስኬታማነት ቀጥሏል።

ዛሬ በይፋ የከፈትነው የኢትዮጵያ ብክለት ቀናሽ እንቅስቃሴ (ግሪን ሞቢሊቲ) 2025 ዐውደ ርዕይና መድረክ ኢትዮጵያ ተፈጥሮን ለመካስና ብክለት ቀናሽ ኢኮኖሚ ለመገንባት የጀመረችው ታሪካዊ ጉዞ ማሳያ ነው።

ይህ ዐውደ ርዕይ አዳዲስ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ቴክኖሎጂዎች ለዕይታ የሚቀርቡበት ከመሆኑም በላይ፤ በመንግሥት፣ በባለሀብቶችና በኅብረተሰቡ መካከል የጋራ ግንዛቤና ትብብር የሚፈጥር መድረክ ነው፡፡

ከአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት ለመውጣት እንደ አረንጓዴ ዐሻራና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ማስፋፋት ያሉ ውጤታማ የአረንጓዴ ልማት ርምጃዎችን እየወሰድን ነው።

ኢትዮጵያ በዘመናዊና አረንጓዴ ትራንስፖርት ዓለምን ለመምራት ዝግጁ ናት፤ ታዳሽ ኃይልን ከዘመናዊ ትራንስፖርት ጋር በማቀናጀትና የካርበን ልቀትን በመቀነስ ኢትዮጵያን በአፍሪካ የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ጉዞ ቀዳሚ እያደረግናት እንገኛለን።

ለትውልዱ በሁሉም መስክ ምቹ ሀገርን ለማስረከብም የአረንጓዴ ብልጽግና ጉዟችንን አጠናክረን ቀጥለናል።

ለዚህ ራዕይ መሳካት የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ግለሰብና ተቋም ዘመኑን የመዋጀት የባህልና የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲሁም ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው።

እኛ ስለ አረንጓዴ ዕድገት የምንጨነቀው ስለ መጪው ትውልድ ስለምንጨነቅ ነው።

መንግሥት ለዚህ ዓላማ ስኬታማነት የመሪነት ሚናውን አጠናክሮ ይቀጥላል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top