በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት የቡድን መሪዎችን ፈለቀ የሻምበል እና ጎምበል ሳህሌን ጨምሮ 22 ታጣቂዎች የቡድንና የነብስ ወከፍ መሳሪያወችን በመያዝ መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላም ተመልሰዋል።
ታጣቂወቹን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፋሲል ሰንደቁን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችና የወረዳ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሰላም የገቡ ታጣቂዎችም የወረዳውን ዘላቂ ሰላም እና ልማት ለማረጋገጥ የድርሻቸውን እንደሚወጡ በመግለፅ ከዚህ በፊት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የበደሉትን ሕዝብ ለመካስ መዘጋጀታቸውንም ጨምረው መናገራቸውን ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

