የአማራ ክልል ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

(ታህሳስ16/2018)፡-የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር ፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው።

ዛሬ የተጀመረው የምክር ቤቱ ጉባዔ በሁለት ቀናት ቆይታው የክልሉ ትምህርት ቢሮ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

በዚህም በትምህርት አጀማመርና እስካሁን በተከናወኑ ተግባራትና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ትኩረት አድርጎ በመምከር የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል።

የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የፋይናንስ ህጋዊነት፤ የክዋኔ ኦዲት ግኝቶችንና የተሰጡ የማሻሻያ ሃሳቦችን የሚያሳይ የተጠቃለለ ሪፖርት ለምክር ቤት አላት ቀርቦ ወይይት ይደረግበታል።

በመጨረሻም ልዩ ልዩ አዋጆች ለምክርቤቱ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top