በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂ ሃይሎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ገቡ፤

በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ በጉባይና ሌንጫ ቀበሌዎች የትጥቅ ትግልን አማራጭ አድርገው በጫኬ ሲቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በሰላም ገብተዋል።

እስካሁን በዱር በገደሉ ስንገላታ ቆይተናል ያሉት ታጠቂዎቹ፦ ሌሎች በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎችም የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እንዲገቢ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን የሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደረሰ አዱኛ በበኩላቸው፦ በዞኑ ሰላምን ለማፅናት በሚደረገው ህዝባዊ ውይይት ጎን ለጎን በዛሬው ዕለት መተማ ወረዳ ጉባይ-ጀጀቢት እና ሌንጫ ቀበሌዎች ሲቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ከእነሙሉ ትጥቃቸው በሰላም መግባታቸውን ተናግረዋል።

ሌሎች በአካባቢው በህገወጥ መንገድ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላትም የመንግስትን የሰላምን ጥሪ እንዲቀበሉ የመምሪያ ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።

የታጣቂዎቹ ሲገቡ በዞን፣ ወረዳው እና በመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በሀገር ሽማግሌዎች ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ከምዕራብ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top