በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ በእንቃሽ እና ቀንባዳ ቀበሌ አካባቢ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 25 ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበላቸው ተገለጸ።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉ የታጣቂዎች እንደተናገሩት፦ የበደሉትን ሕዝብ ለመካስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ጫካ ላይ ለሚገኙ ታጣቂዎች የሰላምን መንገድ መምረጥ አዋጪ መሆኑን መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከወገራ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

