ባሕርዳር ጸጋዋ ብዙ ነው። በተፈጥሮ ሐብት የታደለች፤ በጣና ሀይቅና አባይ ወንዝ ዳርቻ ላይ የተመሠረተች ከተማ ነች።
ከተማዋ የትምህርትና የቱሪዝም ኮንፈረንስ ከተማ ነች። የቱሪዝም መዳረሻ የሚሆኑ በርካታ የመስህብ ስፍራዎች አሏት።
የጣና ሀይቅ ገዳማት፣ የቤዛዊት ቤተመንግሥት፣ ጭስ አባይ ፏፏቴና ሌሎች በርካታ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ይገኙባታል።
ከተማዋን ካላት እምቅ የተፈጥሮ ጸጋ ጋር በማስተሳሰር ዘመናዊና ተወዳዳሪ ከተማ ለማድረግ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ይበልጥ እንድትዋብ አድርጓታል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ በተሰራው የኮሪደር ልማት ስራ ባሕርዳርን ከጣና ሐይቅ ጋር አስተሳስሮ ለነዋሪዎቿ ምቹ ውብና ጽዱ፤ ለጎብኝዎች ደግሞ ሳቢና ማራኪ ከተማ መሆን የምትችልበትን እድል ተፈጥሯል።
በከተማዋ ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን ከባሕርዳር ከተማ በተጨማሪ በሌሎች በክልላችን ከተሞችም የኮሪደር ልማት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

