በምሰራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ጫካ የነበሩ ታጠቂዎች መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ደብረ ማርቆስ ከተማ ገብተዋል።
መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀበለው የገቡት አማኑ ሞላ ላመስን፣ ዘውዱ ስማቸው ደርሰህ፣ እድሚያለም አስማማው ብዙነህ፣ ውዱ ጋሻው ነጋ ሲሆኑ የተለያዩ አደረጃጀት መሪ የነበሩ ናቸው።
የመንግስትን የሠላም አማራጭ በመጠቀም 2 ጥቁር ክላሽ እና 2 ሰደፍ ክላሽ ከ10 ካዘና እና ከ117 ጥይት ይዘው መግባታቸውን ከደብረ ማርቆስ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

