በሰሜን ጎንደር ዞን በዋልድባና ጠለምት አካባቢ ሲንቀሳቀስ የነበረ በሃጎስ መስፍን የሚመራው ቡድን አመራርና አባላት የሰላም አማራጩን በመቀበል በቀጠናው ለሚገኘው 10ኛ ዕዝ ዓባይ ኮር መብረቅ ክፍለጦር ከነሙሉ ትጥቃቸው በሰላም ገብተዋል፡፡
ቡድኑ የሰላም አማራጩን ተቀብሎ በሰላማዊ መንገድ እንዲገባ በሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ስራ መሰራቱ እና ዕዙም ከበላይ አካል የተሰጠውን አቅጣጫ መነሻ በማድረግ በአካባቢው የሚገኙ ክፍሎች ጥብቅ ክትትል እንዲያደርጉ በማድረግ ታህሳስ 04 ቀን 2018 ዓ.ም የሠላም ጥሪውን ተቀብለው እጅ መስጠታቸውን የዓባይ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ሃሽም ኢብራሂም ገልፀዋል፡፡
170 የታጣቂ ቡድኑ አባላት እጅ የሠጡ ሲሆን የተለያዩ ዓይነት መሣሪያዎችን እና ተተኳሾችን ይዘው ገብተዋል፡፡
የአካባቢው ህዝብም በሰላም ለገቡ የቡድኑ አባላት አቀባበል በማድረግ ሰላም ወዳድነቱን አሳይቷል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

